loading
ላሊበላን እንታደግ በሚል ነዋሪዎች አሁን በከተማዋ ሰልፍ ወጥተዋል

አርትስ 27/01/2011
የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናትን ከፀሀይ እና ዝናብ ለመከላከል ታስቦ በጊዜያዊነት ለአምስት ዓመታት የተሠሩት መጠለያዎች አሁን 11ኛ አመታቸውን እያስቆጠሩ እንደሆነ የአብያተክርስቲያናቱ አስተዳደሮች ነግረውናል ፡፡
አርትስ ቲቪ በቦታው ተገኝቶ እንደተመለከተው የሰልፈኞቹ ጥያቄዎች በዮኔስኮ እና በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ የተገነቡት ጊዜያዊ መጠለያዎች ከ ሶስት ቶን በላይ መመዘናቸው፤ መጠለያዎቹን ደግፈው የያዙት የብረት ምሰሶዎች መሬቱን እየሰነጣጠቁ በመሆኑ ፤መጠለያዎቹ ተነስተው በሌላ ቅርሶቹን በማይጎዳ መጠለያ እንዲተኩ እና የተሰነጣጠቁ እና የመፍረስ አደጋ የተጋረጠባቸው የቅርሶቹ አካል በአፋጣኝ እንዲታደስ የሚሉት ናቸው ፡፡
የአብያተ ክርስቲያናቱ መሪ አባቶች እንደገለፁት በቅርሶቹ ዙሪያ በአ.አ ዮኒቨርሲቲ ፣በዮኔስኮ እና ሌሎች አካላት የቀረቡ ጥናቶች አካባቢዉ ለመሬት መንቀጥቀጥ የተጋለጠ መሆኑን ጠቁመዋል ነገርግን ጊዜያዊ መጠለያዎቹን የያዙት እና መሬት ላይ የተተከሉት ብረቶች መሬቱን እየሰነጣጠቁት መሆኑን ተመልክተናል፡፡
የላሊበላ ከተማ ም/ከንቲባ አቶ ሀይሌ ንጋቴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት መሠረት በአንፃሩ መጠለያዎቹን ለማንሳት እና ለእድሳቱ 300 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ የተነገረ ሲሆን በመንግሥት በጀት ተብሎ ለከተማዋ የተላከው ደብዳቤ 20 ሚለዮን ብር እንደሆነ ነግረውናል ፡፡
ከበርካታ የውጭ ቱሪስቶች አገሪቱ የምታገኘው ገቢ ላሊበላን ከመሰሉ አበይት ቅርሶች ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *