ሰሜን ኮሪያ ከአሁን ቀደም ይፋ ያላደረገቸው የሚሳኤል ጣቢያ አላት ተባለ
ሰሜን ኮሪያ ከአሁን ቀደም ይፋ ያላደረገቸው የሚሳኤል ጣቢያ አላት ተባለ
ይህ ዜና የተሰማው ፕሬዝዳዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኪም ጆንግ ኡን ጋር በመጭው የካቲት ወር ተገናኝቸ ሁለተኛውን ዙር ውይይት ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ካሉ ከሶስት ቀናት በኋላ ነው፡፡
ሴንተር ፎር ስትራቴጂክ ኤንድ ኢንተርናሽናል ስተዲ የተባለ ተቋም ባወጣው ሪፖርት ከአሁን በፊት ፒዮንግያንግ አወድማቸዋለሁ ብላ ድርድር ውስጥ ካስገባቻቸው የሚሳኤል ጣቢያዎች ውጭ የሆነ የባለስቲክ ሚሳኤል ዋና መስሪያ ቤት ተገኝቷል ብሏል፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው ሰሜን ኮሪያ 20 የሚሳኤል ጣቢያዎቿን በድርድር አውድማለሁ ባለቸው መሰረት ተግባራዊ ብታደርግ እንኳ ይሄኛው ጣቢያ በራሱ ለተፈላጊው ግዳጅ ዝግጁ ነው፡፡
ከአሁን ቀደም ይፋ ያልተደረገው ይሄ የሚሳኤል ጣቢያ በ18 ስኩየር ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባ ሲሆን ደቡብ ኮሪያን፣ ጃፓንን፣ እንዲሁም የአሜሪካ የግዛት አካል የሆነችውን የጉዋምን ደሴት በማካለል የመወንጨፍ ብቃት አለው ተብሏል፡፡
አዲስ ይፋ የሆነውን ሪፖርት በተመለከተ ከአሜሪካ በኩል እስካሁን የተሰጠ አስተያየት ባይኖርም የፖለቲካ ተንታኞች የሰሜን ኮሪያ ድርጊት የትራምፕን አስተዳደር ቅር እንደሚያሰኝ ከወዲሁ እየተናገሩ ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ኪም ሲንጋፖር ላይ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ተገናኝተን ከተወያን ወዲህ እኛ ቃላችንን ጠብቀናል፤ አሜሪካ ግን ስምምነታችንን ተግባራዊ ማድረግ ተስኗታል በማለት ወቀሳ ሲሰነዝሩ ተደምጠው ነበር፡፡
ኪም ባአዲሱ ዓመት ዋዜማ ለህዝባቸው ባደረጉት ንግግር አሜሪካ ቃሏል ጠብቃ ማእባችንን የማታነሳ ከሆነ አዲስ መንገድ ለመከተል እንገደዳለን ማለታቸው ይወሳል፡፡