loading
ሶስተኛው የኢጋድ እና የአውሮፓ ህብረት የሚኒስትሮች የጋራ ስብሰባ ተካሄደ

ሶስተኛው የኢጋድ እና የአውሮፓ ህብረት የሚኒስትሮች የጋራ ስብሰባ ተካሄደ

ሶስተኛው የኢጋድ እና የአውሮፓ ህብረት የሚኒስትሮች የጋራ ስብሰባ በትናንተናው በቤልጂየም ብራሰልስ ተካሂዷል።

ሁለቱ ወገኖች በጋራና በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ለቀጠናው ያለውን አዎንታዊ ጠቀሜታ፣ የሶማሊያ እንዲሁም የደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደት ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ ውይይት አድርገዋል።

በአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ ውህደት መመስረት እና በዓለም ላይ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ያለውን ፋይዳ በተመለከተም ተወያይተዋል።

የአውሮፓ ህብረት በቀጠናው ልማት፣ ሰላም እና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የሚያደርገውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በውይይቱ ተገልጿል።ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደጠቆመው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *