loading
ሽ ጂፒንግ በቻይና ኢኮኖሚ የትኛውም ወርቃማ ህግ አይሰራም አሉ

አርትስ 10/04/2011

 

ቻይና የኢኮኖሚ ሪፎርም ያደረገችበትን 40ኛ አመት በማክበር ላይ ናት፡፡

የቻይናው ፕሬዚዳንት  ሽ ጂፒንግ የሀገራቸው የኢኮኖሚ ፖሊሲ በማንኛውም አካል ሊመራ እንደማይችል አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ  በኮሚኒስት ፓርቲያቸው አባላት ፊት ባደረጉት ንግግር ከ40 ዓመት በፊት  ቻይና በሯን ክፍት በማድረጓ  አሁን ላይ የአለምየኢኮኖሚ ማዕከል ሆናለች ብለዋል ፡፡

ሀገራቸው  የመንግስት መር የኢኮኖሚ እድገት እንዲመጣ ድጋፍ እንደምታደርግ የገለፁት ሽ   ድጋፉ ለግሉ ዘርፍም ይሰራል ብለዋል፡፡

ቻይና በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ1978 የሀገሪቱ በኢኮኖሚ ፖሊሲዋ ላይ ለውጥ አድርጋ ቻይና ከ40 አመት በፊት  አመታዊ የምርት መጠኗ መቶ ሃምሳ ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡

ከሃያ አመታት በኋላ ግን ይህ አሀዝ የ12 ትሪሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በመሆኑም ቻይና  በንግዱ ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ ተፅዕኖ መፍጠር ችላለች፡፡

ለአፍሪካ ሀገራት የምታቀርበው የብድር መስጫ ድርድር በኢኮኖሚ ምሁራን ዘንድ በጤናማ መልኩ አይታይም፡፡

ምክንያቱ ደግሞ ሀገራቱን ከፍተኛ የእዳ ጫና ውስጥ የሚከት ስትራቴጂ በመሆኑ  ሳይወዱ ለቻይና ፍላጎት  እንዲገዙ ያደርጋል የሚል ነው፡፡

ፕሬዚዳንቱ  በንግግራቸው ቻይና ተጨማሪ የኢኮኖሚ ለውጦችን ታደርጋለች ቢሉም ዝርዝሩን ከመናገር  ግን ተቆጥበዋል ፡፡

ቻይና ከአሜሪካ ጋር በንግድ ጦርነት ላይ በምትገኝበት ወቅት የተደረገው የፕሬዚዳንቱ ንግግር አሜሪካም ስለ ለውጥ እንድታስብ ጫናለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል። ዘገባው የሲ.ጂ.ቲኤን ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *