loading
በማህበረሰብ አቀፍ የኤች.አይ.ቪ ተጽእኖ ላይ የተደረገ የዳሰሳ ጥናት ይፋ ሆነ

በማህበረሰብ አቀፍ የኤች.አይ.ቪ ተጽእኖ ላይ የተደረገ የዳሰሳ ጥናት ይፋ ሆነ

አርትስ 02/04/2011

ጥናቱ በአገር አቀፍ ደረጃ ባሉ ከተሞች ዕድሚያቸው ከ15-64 ዓመት ከሆኑትና ኤች.አይ.ቪ ካለባቸው ሰዎች ውስጥ 70% የሚሆኑት  የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ መቀነሱን አሳይቷል፡፡

ነገርግንዕድሜያቸውከ15-64 ዓመትየሆኑኤች.አይ.ቪበደማቸውካለባቸውወንዶችውስጥኤች.አይ.ቪእንዳለባቸውየሚያውቁትከሁለትሶስተኛበታች (62%) ናቸው ብሏል፡፡

በጥናቱ ይፋዊ ስነ-ስርዓት የተገኙት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ  ዶ/ር አሚር አማን እንደተናገሩት ባለፉት አስራ ሰባት ዓመታት በኤች.አይ.ቪ መከላከልና መቆጣጠር ላይ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመው ቀደም ሲል በየዓመቱ በቫይረሱ ይያዙ ከነበሩት 81 ሺህ ሰዎች አሁን ላይ ወደ 15 ሺህ ዝቅ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡ በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔውም ከነበረው 5.8% ወደ 0.9% ማውረድ የተቻለ ቢሆንም አሁንም ችግሩ አሳሳቢ ስለሆነ ባለፉት ዓመታት በተገኙ ውጤቶች ሳንዘናጋ ልዩ ትኩረት ሰጥተን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ጥናቱ በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስተባባሪነትና በአሜሪካ ፕሬዝዳንት አስቸኳይ ጊዜ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ዕቅድ የገንዘብ ድጋፍ የተካሄደ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጠቁሟል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *