loading
በዲሞክራቲክ ኮንጎ የጣሊያን አምባሳደር በጉዞ ላይ እያሉ በደረሰ የታጣቂዎች ጥቃት መገደላቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 16፣ 2013 በዲሞክራቲክ ኮንጎ የጣሊያን አምባሳደር በጉዞ ላይ እያሉ በደረሰ የታጣቂዎች ጥቃት መገደላቸው ተሰማ:: አምባሳደር ሉካ አታናሲዮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተሸከርካሪ በሚጓዙበት ወቅት ነው ከግል ጠባቂያችው ጭምር ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመትተው የተገደሉት፡፡ አምባሳደሩን እና አጃቢያቸውን ሲያጓጓዝ የነበረውና የሀገሬው ተወላጅ የሆነው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ድርጅት ሾፌርም በደረሰው ጥቃት ተገድሏል ነው የተባለው፡፡

የዓይን እማኞች እንደተናገሩት አምባሳደሩን ከመኪና አስወርደው አፍነው ወደ ጫካ በመውሰድ ነው የገደቸሏው፡፡ ጥቃቱ የደረሰው የምስራቃዊ ኮንጎ ግዛት ዋና መዲና በሆነችው ሩትሹሩ ከተማ በዓለም ምግብ ፕሮግራም እገዛ የተገነባ ትምህርት ቤት ለመጎብኘት በመጓዝ ላይ እንዳሉ ነው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደገዘገበው የዲሞክራቲክ ኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቱምባ ንዜዛ ከተከሰተው አሳፋሪ ተግባር ጀርባ እነማን እንዳሉ በፍጥነት አጣርተን ለጣሊያን መንግስት እናሳውቃለን ብለዋል፡፡

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በበኩሉ አካባቢው ለእንደዚህ ዓይነት ጥቃት የተጋለጠ መሆኑ እየታወቀ የግዛቷ ባለስልጣናት ለምን ጥበቃ እንደማያደርጉ ማብራሪያ እንደሚፈልግ ተናግሯል፡፡ የጣሊያኑ ፕሬዚዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ በአምሳደሩ ላይ የተፈፀመውን የጭካኔ ግድያ በፅኑ ያወገዙ ሲሆን ጠሊያናያንም ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *