አዲሱ ተገኘ የተባለው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ለዓለም ሀገራት ስጋት እየሆነ ነው ተባለ ::
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013 አዲሱ ተገኘ የተባለው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ለዓለም ሀገራት ስጋት እየሆነ ነው ተባለ :: በዚህም አዲሱ ቫይረስ በመጀመሪያ ታይቷል ከተባለበት ከእንግሊዝ ወደ ተለያዩ አገራት የሚደረጉ በረራዎችን ታግደዋል። የአውሮፓ ሕብረት አባል አገራት በዚህ ዙሪያ የጋራ ፖሊሲ ለማውጣት እየተወያዩ ነው የተባለው፡፡ ሲሆን ዴንማርክ ውስጥም አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በመታየቱ ስዊድን ወደ ዴንማርክ የሚደ ረገዉንም ጉዞ አግዳለች።
የወረርሽኙ ዝርያው በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰራጭ በመሆኑ ቀድሞ ከነበረዉ ቫይረስ ይልቅ ጎጂ ስለመሆኑ እየተነገረ ቢሆንም እስካሁን ግን በተጨባጭ የተገኘ መረጃ የለም ተብሏል። የዓለም ጤና ድርጅት፥ አዲሱ የቫይረስ ዝርያ በወረርሽኙ ዝግመተ ለውጥ ሂደት የሚጠበቅ ነው ብለዋል። የእንግሊዝ የጤና ሚንስትር ጸሐፊ ማት ሀንኮክ አዲሱ ዝርያ ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል ቢሉ ም ማይክ ራይን ግን አዲሱ ዝርያ ከቁጥጥር አልወጣምብለዋል።
በእንግሊዝ ከተገኘው የቫይረስ ዝርያ የተለየ አዲስ ዝርያ በደቡብ አፍሪካም ተገኝቷል። የደቡብ አፍሪካ ተጓዦች ላይ እገዳ እየተጣለም ነው። እስካሁን የአዲሱ ቫይረስ ዝርያ በዴንማርክ፣ አውስትራሊያ፣ ጣልያን እና ኔዘርላንድስም ተገኝቷል።