አጫጭር ዜናዎች…
የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን፤ የ29 ዓመቱ ዌልሳዊ አጥቂ ጋሪት ቤል የወደፊት ቆይታ የውድድር ዓመቱ ማብቂያ ላይ እንደሚወሰን ተናግሯል፡፡
ተጫዋቹ ከማንችስተር ዩናይትድ እና የቀድሞ ክለቡ ቶተንሃም ጋር ስሙ በሰፊው ተያይዟል ሲል ቶክ ስፖርት አስነብቧል፡፡
……………………..
ማንችስተር ዩናይትድ ደግሞ ከሪያል ማድሪድ በኩል የሚሰማውን የፈረንሳያዊውን ፖል ፖግባ እናዛውር ጥያቄ፤ በስምምነቱ ውስጥ ከገንዘብ በተጨማሪ የቤልን አሊያ የቶኒ ክሮስን ፊርማ እንዲካተት እንደሚጠይቅ አስ በዘገባው አመላክቷል፡፡
……………….……….
የእንግሊዙ ሌስተር ሲቲ ከሞናኮ በውስት ውል ያስፈረመውን ቤልጂየማዊ ዮሪ ቴሊማንስ በ40 ሚሊዬን ፓውንድ ሂብ በቋሚነት ለማስፈረም እያጤነው እንደሆነ ደይሊ ሜል ጠቁሟል፡፡
………………………..
የማንችስተር ዩናይትዱ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር የክሪስታል ፓላሱን የ21 ዓመቱን እንግሊዛዊ የተከላካይ መስመር ተጫዋች አሮን ዋን- ቢሳካ ለማስፈረም፤ 35 ሚሊዬን ፓውንድ ዋጋ የማቅረብ እቅድ አለው ሲል ሜይል አስነብቧል፡፡
የቀያይ ሰይጣኖቹ አለቃ ኦሌ በመጪው ክረምት ከክለቡ ይለቃል ተብሎ የሚጠበቀውን አንቶኒዮ ቫሌንሲያ ለመተካት ዋን- ቢሳካ ቀዳሚ ኢላማው እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
………………………..
የ30 ዓመቱ የግራ ተከላካይ መስመር ተሰላፊ ተጫዋች ብራዚላዊው ማርሴሎ ዚዳን የማድሪድ አሰልጣኝ ሁኖ በድጋሜ ወደ ቤርናቤው መመለሱን ተከትሎ፤ በክለቡ የመቆየት ውጥን እንዳለው አስ አስታውቋል፡፡
……………………………….
አርሰናል ደግሞ በጉዳት ለሚገኘው የአጥቂ ተጫዋቹ፤ እንግሊዛዊው ዳኒ ዌልቤክ አዲስ ኮንትራት ሊሰጠው እንደሚችል ኢንዲፔንዴንት ዘግቧል፤ የ28 ዓመቱ ተጫዋች የውድድር ዓመቱ ከማብቃቱ በፊት ወደ ልምምድ ሊመለስ እንደሚችል ተነግሯል፡፡
…………………………………
ራፋኤል ቫራን ሪያል ማድሪድን በክረምቱ ሊለቅ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡
እና ጣሊያኑ ካልሺዮ መርካቶ ዘገባ ዩቬንቱስ በክረምቱ ቅድሚያ ከሚያስፈርመው የተከላካይ መስመር ተጫዋች ቫራን አንዱ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
የሴሪ ኤው መሪ እያረጁ የሚነኙቱን ሊዮናርዶ ቦኑቺ እና ጆርጂዮ ኬሊኒ የመተካት ውጥን አላቸው፡፡