loading
ኢትዮጵያ 300 ሺህ ሲኖፋርማ የኮቪድ19 ክትባት ከቻይና ተረከበች
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2013 ኢትዮጵያ 300 ሺህ ሲኖፋርማ የኮቪድ19 ክትባት ከቻይና መንግስት ተረከበች። በኢትዮጰያ የቻይናው አምባሳደር ዣሆ ዢያን ኢትዮጵያ ቻይና በኮቪድ19 በተጠቃች ጊዜ ወዳጅነቷን ያሳየች ጠንካራ አጋር መሆኗን ተናግረዋል። አምባሳደሩ በቀጣይም ቻይና መሰል ድጋፎችን ታደርጋለችም ነው ያሉት፡፡
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው ቻይና ዛሬ ካደረገችው ድጋፍ በተጨማሪ ከዚህ ቀደም የኮቪድ19 መከላከያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጓን አስታውሰዋል፡፡ ዛሬ የተደረገው ድጋፍም ሃገሪቱ የጀመረችውን የክትባት ሂደት ለማጠናከር ያግዛል ብለዋል። ሚኒስትሯ አሁን ላይ ያለውን ስርጭት ለመግታት ክትባት ብቻውን በቂ ስላልሆነ ህብረተሰቡም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። ምንጭ FBC.

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *