ከህገወጦች የተነጠቁ 120 የቀበሌ ቤቶችና 64 የመስሪያ ቦታዎች ለችግረኞች ተሰጡ
አርትስ 12/04/2011
ለችግረኞች የተላለፉት የቀበሌ ች በጉለሌ ክፍለ ከተማ የሚገኙና ከዚህ ቀደም በህገ ወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ ናቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደገለጸው ቤቶቹና የመስሪያ ሼዶቹ በህገወጥነት የተያዙ መሆኑ የታወቀው ህብረተሰቡበማሳተፍ ጥቆማ እንዲሰጥ በመደረጉ ነው።
ከዚህ በተጨማሪም ኢ-መደበኛ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊነት ለማምጣት ክፍለ ከተማው ባካሄደው ጥናት በአምስት ሳይቶች 1ሺህ 46 ሰዎች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉንም ከከንቲባው ፅህፈት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።