loading
ካቢላ ስልጣን ብለቅም ከፖለቲካ አልርቅም አሉ

ካቢላ ስልጣን ብለቅም ከፖለቲካ አልርቅም አሉ

አርትስ 01/04/11

የዲሞከራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ በመጭው ምርጫ እንደማይሳተፉ ቀድመው አሳውቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ የሀገራቸው ህገ መንግስት በሚፈቅደው መሰረት ከስልጣናቸው መውረድ የነበረባቸው በ2016 ቢሆንም አስከ 2019 በራሳቸው ፈቃድ አራዝመውታል፡፡

አሁን ኮንጎ በመጨው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት በመገባደጃ ላይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ስታካሂድ የ47 ዓመቱ ላውረነረ ካቢላ አይወዳሩም፡፡

ከሮይተርስ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ካቢላ ከዚህ በኋላ የኔ ሚና የሚሆነው የሀገሬን ፖለቲከኞች ማማከር ነው ብለዋል፡፡

የአባታቸውን መገደል ተከትሎ ወደ ስልጣን የመጡት ጆሴፍ ካቢላ ሀገሪቱን መምራት ከጀመሩ ወዲህ በ2019 የመጀመሪያው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡

በ29 ዓመታቸው ስልጣን ላይ ወጥተው በቤተ መንግስት የጎለበሱት ካቢላ በስልጣን ላይ በቆዩበት ዘመን የሚቆጩበት ወቅት ነበረ ወይ ተብለው ሲጠየቁ ሁሉም ነገር የሆነው በምክንያት ስለሆነ አንዳች ፀፀት አይሰማኝም ብለዋል፡፡

ስለምርጫው መራዘም ለተለሳላቸው ጥያቄ አሁን ዋናው ትኩታችን ምርጫው በሁሉም ረገድ የተዋጣለት እንዲሆን ነሮችን ማመቻቸት ነው ብለዋል ፕሬፕዝዳንቱ፡፡

ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ግን በሀገሪቱ ያለው አለመረጋጋት እና የኢቦላ በሽታ ምርጫውን በኣግባቡ ለመታዘብ እንቅፋት እንደሚሆን ይህም ለካቢላ የጥምረት ፓርቲ እንደፈለገ ውጤቱን ለመቀየር ያመቸዋል የሚል ስጋት አድርባቸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *