የሀጂ ተጓዦች ከከባድ ዝናብ ጋር እየታገሉ ነው፡፡
ማንኛውም ሙስሊም በህይዎት ዘመኑ አንድ ጊዜ ሊያሳካው የሚመኘውን የሀጂ ስነ ስርዓት ለመታደም ከ2 ሚሊዮን በላይ አማኞች ሳውዲ አረቢያ ገብተዋል፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው እምብዛም ዝናብ በማታውቀው ሳውዲ አረቢያ እየዘነበ ያለው ነጎድጓዳማ ዝናብ የጎርፍ አደጋና ውሀ ወለድ በሽታ እንዳያደስከትል ተሰግቷል፡፡
የሀገሪቱ የጤና ሚንስቴር ግን እስካሁን ምንም ዓይነት ችግር አላጋጠመም የታየ የህመም ምልክትም የለም የሚል መግለጫ ሰጥቷል፡፡