loading
የመንግስት ንግድ ቤት ተከራዮች የቤቶች ኮርፖሬሽን የወሰነውን የዋጋ ጭማሪ  በድጋሚ እንዲያጤንላቸው መንግስትን ጠየቁ

የመንግስት ንግድ ቤት ተከራዮች የቤቶች ኮርፖሬሽን የወሰነውን የዋጋ ጭማሪ  በድጋሚ እንዲያጤንላቸው መንግስትን ጠየቁ፡፡

ነጋዴዎቹ ይህን የጠየቁት ዛሬ በግሎባል ሆቴል አዳራሽ ባደረጉት የጋራ ውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

በውይይታቸውም ለቤት ኪራይ የተወሰነው ውሳኔ በበቂ ጥናት ላይ ያልተመሰረተ እና በቂ ባለሙያዎችን ያሳተፈ አይደለም ብለዋል፡፡

አቋማችን ጭማሪው አይደረግ የሚል ሳይሆን ተመጣጣኝ ጭማሪ ይደረግ የሚል ነው ብለዋል፡፡

ውሳኔው ነጋዴዎቹ ከቤታቸው የማፈናቀል እንደሚያስከትል፣ የድርጅቶቹን ሰራተኞች ህልውናም አደጋ ውስጥ ሊከት የሚችል ነው ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ ከአዲስ አበባ ብቻ 6 ሺ 635 የመንግስት ቤት ተከራይ ነጋዴዎች ያሉ ሲሆን በስራቸውም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ያስተዳድራሉ። መረጃው የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ነው።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *