loading
የሳርቤት ጎፋ ማዞርያ የፑሽኪን ጎተራ ማሳለጫ ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ።

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 የሳርቤት ጎፋ ማዞርያ የፑሽኪን ጎተራ ማሳለጫ ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ። የመንገድ ፕሮጀክቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎ ክፍት ሆኗዋል፡፡
 
የማሳለጫ የመንገዱ በዘመናዊ መልኩ የተገነባ ሲሆን የአዲስ አበባን ስምና አለም አቀፍ ደረጃዋን በሚመጥን መልኩ የተከናወነ ስለመሆኑ ተገልጿል። የፑሽኪን አደባባይ- ጎፋ ማዞሪያ- ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት 3 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ርዝመትና ከ30 እስከ 45 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን በቻይና ፈርስት ሀይ ዌይ ኢንጂነሪንግ የስራ ተቋራጭ ግንባታው መከናወኑ ተነግሯል።
 
የግንባታው ወጪ ከቻይና መንግስት በተገኘ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ብድር የተሸፈነ ሲሆን በሁለት በኩል 320 ሜትር ርዝመት ያለው ዋሻ፣ የፈጣን አውቶቡስ መተላለፊያ መስመርና ተሽከርካሪዎችን ከስርና ከላይ የሚያሳልፍ ዘመናዊ መንገድ ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *