የነዳጅ እጥረት የተከሰተው ነዳጅን የማሸሽ ህገ ወጥ ተግባር እየተሰራ ስለሆነ ነው ተባለ
የነዳጅ እጥረት የተከሰተው ነዳጅን የማሸሽ ህገ ወጥ ተግባር እየተሰራ ስለሆነ ነው ተባለ
አርትስ 16/02/2011
በኢትዮጵያ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የተከሰተው የነዳጅ አቅርቦት ችግር ሰው ሰራሽ የሆነ ነዳጅን የማሸሽ ህገ ወጥ ተግባር በመከናወኑ እንደሆነ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ተናገረ።
የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ወንድሙ ፍላቴ እንደገለጹት፤ በምርት አቅርቦት ዙሪያ በሚፈጸም ደባ ያለምንም ኢኮኖሚያዊ ምክንያት እጥረት እየተፈጠረ መሆኑን እና ነዳጅ የሚያከፋፍሉ ኩባንያዎች ከተፈቀደላቸው የነዳጅ ማራገፊያ ስፍራ ውጪ በማራገፍ እጥረቱ እንዲፈጠር ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።
ይህ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ባለፉት ሳምንታት የነዳጅ እጥረት እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑን ገልፀው፤ ነዳጅ በጥቁር ገበያ በበርሜልና በጄሪካን ጭምር እንዲሸጥ በማድረግ በኮንትሮባንድ የመነገድ ተግባርና ነዳጅ መልሶ ከአገር እንዲወጣ የማድረግ ህገ ወጥ ተግባር መስተዋሉን እና ነዳጅ የሚያጓጉዙ ኩባንያዎች ነዳጅ ከማደያ ውጪ መሸጥ እንደሌለባቸው አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪ በማድረግ ወደ አገር ከምታስገባቸው ምርቶች ውስጥ አንዱ ነዳጅ ሲሆን በአመት 3 ቢሊዮን የአሜረካ ዶላር ታወጣለች።