loading
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ማስተዋወቂያ መድረክ በቻይና ተካሄደ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ማስተዋወቂያ መድረክ በቻይና ተካሄደ

በመድረኩ በግል ሆስፒታል ግንባታ፣ በህክምናና መድሃኒት ማምረት ዘርፎች በኢትዮጵያ ስላሉ

የኢንቨስትመንት እድሎች ዙሪያ ለቻይና ባለሀብቶች ገለጻ ተደርጓል።

የኢትዮጵያን ልዑካን የመሩት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ኢትዮጵያ ለዘርፉ ልማት ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኗን ጠቅሰው የሚሰጡ ማበረታቻዎች፣ የገበያ አቅርቦት፣ አመቺ ፖሊሲዎችና የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ለአብነት አንስተዋል።

በአፍሪካ እያደገ ያለው የህዝብ ቁጥርና በህክምና ዘርፍ ያለው ፍላጎት እየጨመረ መሆኑን ገልጸው ለዚህም ኢትዮጵያ ለቻይና ኩባንያዎች አይነተኛ መዳረሻ ነች ብለዋል።

እንደ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ገለፃ የዦኩ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኪን ሸንጂን በቻይና መንግስት የተያዘው የቤልት ኤንድ ሮድ ትልም በኢትዮጵያና በከተማዋ ያለውን ትብብር ያሳድገዋል ብለዋል።

በሄናን ከተማ የቻይና አፍሪካ ቢዝነስ ማህበር ሊቀመንበር ው ዮንግ በመጪው ግንቦት 30 የቢዝነስ ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚያቀና አስታውቀዋል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *