የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ60 ሺህ አገልግሎት ፈላጊዎችን ችግር የሚፈታ የትራንስፎርመር ግዢ ሊፈጽም ነው
አርትስ ታህሳስ 12 2011
ተቋሙ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጡ በቁጥር 4 ሺህ 978 የሆኑ 17 ዓይነት ትራንስፎርመሮችን ለመግዛት ከሁለትሃገር በቀል ድርጅቶች ጋር የግዥ ውል ፈፅሟል፡፡
ስምምነቱ ለአንድ አመት የሚቆይ ሲሆን ግዢው ከ50 እስከ 1 ሺህ 250 ኪሎ ቮልት አምፒር አቅም ያላቸውን ትራንስፎርመሮች ያካትታል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ እንደተናገሩት የግዥ ስምምነቱ በማህበረሰቡዘንድ በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የኤሌክትሪክ ሃይል ፍላጎት ለማርካት ትልቅ ጠቀሜታ አለው ።
ስምምነቱን የፈፀሙት የሁለቱ ተቋማት ተወካዮች በበኩላቸው፥ ጥራት ያላቸው ትራንስፎርመሮችን በውሉ በተቀመጠውየጊዜ ሰሌዳ መሰረት አምርቶ ለማስረከብ ከፍተኛ ርብርብ እናደርጋለን ብለዋል።
ግዢው የህብረተሰቡን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ለማሟላት ወሳኝ እርምጃ ነው ተብሏል ፣ ዜናው የኢዜአ ነው።