loading
የዚምባቡየ ፍርድ ቤት መንግስት የዘጋውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲከፍት ትእዛዝ ሰጠ

የዚምባቡየ ፍርድ ቤት መንግስት የዘጋውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲከፍት ትእዛዝ ሰጠ

በዚምባቡየ የነዳጅ ዋጋ ማሻቀቡን ተከትሎ በሀገሪቱ በተቀሰቀሰው አመፅ ስጋት የገባው የፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ አስተዳደር የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ማድረጉ በሀራሬ ሌላ ቁጣን አስነስቷል፡፡

ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው በዚምባቡየ የኢንተርኔት አገልግሎት ከተቋረጠ ሳምንት አስቆጥሯል፡፡

በዚህም ምክንያት ተቃውሞው እየበረታ ሄዶ በሰልፈኞቹ እና በፖሊስ በካከል በተፈጠረ ግጭት 12 ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል፡፡

የዚምባቡየ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኢንተርኔት  መዘጋቱ አንድም ብጥብጡን ያባብሰዋል በሌላ በኩል ደግሞ መረጃ የማግኘት መብትን ይጋፋል በሚል መንግስት በአስቸኳይ አገልግሎቱን እንዲጀምር ሲል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

የዚምባቡየ ንግድ ማህበር ዋና ፀሀፊ ጃት ሞዮን ለአባሎቻቸው ከቤት ያለመውጣት አመፅ አደንዲያደርጉ ቀስቅሰዋል በሚል ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡

መንግስት በሀገሪቱነ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና አክቲቪስቶች አመፁን በማባባስ ተግባር ለይ ተሰማርተዋል በማለት ወቀሳ አቅርቦባቸዋል፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲዎች በበኩላቸው  አባላት እና ደጋፊዎቻችን በምናንጋግዋ መንግስት  ሰዎች መዋከብ እና እንግልት እንዲሁም እስራ እየተፈፀመባቸው ነው በማለት መንግስትን ይከሳሉ፡፡

በዚምባበቡየ የተፈጠረው የዋጋ ግሽበት የዜጎችን የመግዛት አቅም በከፍተኛ ደረጃ አዳክሞታል ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *