loading
የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል በወንጀል የሚፈለጉትን ሰዎች ለሕግ ለማቅረብ እየሰራ መሀኑን የ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽቤት አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል በወንጀል የሚፈለጉትን ሰዎች ለሕግ ለማቅረብ እየሰራ መሀኑን የ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽቤት አስታወቀ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በትግራይ ክልል ሲካሄድ የነበረው የሕግ ማስከበር ዋናኛ ምዕራፍ መጠናቀቁን ገልጾ፣ የፌዴራል መንግስት በክልሉ በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን ለሕግ ለማቅረብ፣ እንዲሁም በአከባቢው ሕግና ስርዓት እንዲኖር እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡

ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ እንደሚደረግ የገለጸው ጽ/ቤቱ፣ ድንበር አቋርጠው ለመሸሽ የተገደዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም መንግስት እየሰራ መሆኑ አስታውቋል፡፡ በትግራይ ክልል በህወሃት ቡድን የወደሙ የትራስፖርትና የቴሌኮሚዩኒኬሸን አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተለመደውን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

የህወሃት ቡድን በሚገባ የተሸነፈ እና የደፈጣ ውግያ ለማድረግ ምንም አቅም የሌለው መሆኑ እየታወቀ ቡድኑ ግን ከነሙሉ አቅሙ እንዳለና ስልታዊ ማፈግፈግ አድርጎ የደፈጣ ውግያ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን የሚያትቱ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ሲነዛ መቆየቱ ተገልጿል፡፡ ቡድኑ ለዓለም የተለያዩ የሐሰት ውንጀላዎችን በማቅረብና የሕግ ማስከበር ዘመቻው ዓለም አቀፍ መልክ እንዲይዝና ከተጠያቂነት ለመምለጥ ጉዳዩ ወደ ድርድር እንዲወሰድ ፍላጎት አሳይቶ እንደነበርም      ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

የህወሃት ቡድን በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጥቃት ከመፈጸሙም ባሻገር በማይካድራ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ፣ እንዲሁም ወደ ባህርዳርና ጎንደር ጅምላ ጨራሽ የጦር መሳሪያ መላኩ ለሰላማዊ ዜጎች ምንም ግድ የሌለው ቡድን መሆኑን ግልጽ ያደርጋል ተብሏል፡፡ ለዜጎች ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑን የገለጸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ በትግራይ ክልል በተደረገው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች እንዲሁም በክልሉ
በስደተኞች ካምፕ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላልሆኑ ስደተኞች ድጋፍ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት ከሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማትና ከመንግስታቱ ድርጅት ኤጀንሲዎች ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *