loading
ግምታዊ ዋጋቸው ከ1.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ 

ግምታዊ ዋጋቸው ከ1.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ስምንት መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ አርባ (867,040) ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎችን ከአሮጌ ብረታ ብረት ጋር ኮድ 3- A30745 አአ በሆነ FSR ተሸከርካሪ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞከር በጉምሩክ ስራተኞች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ አልበረከቴ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ ተይዟል፡፡ በወቅቱ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተይዘው አስፈላጊው የማጣራት ስራ እየተሠራ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው፡፡

በተያያዘ ዜና መጋቢት 15/2011 ጨለማን ተገን በማድረግ ኮድ 2 96913 አአ የሚል የሀሰት ታርጋ የለጠፈ ቪትዝ ተሸከርካሪ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሲል ቶጎጫሌ መስመር በቁጥጥር ስር መዋሉ የተገለጸ ሲሆን፤ ኮድ3-05607 ሱማ ሻምፖ ተሸከርካሪም 750 ሺ ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው 1250 ጀሪካን ባለ 20 ሊትር የምግብ ዘይት ወደ ጅግጅጋ ሲገባ ቀብሪበያሕ መስመር በፌደራል ፖሊስ አባለት፣ በአድማ ብተናና በጉምሩክ አባላት መያዙን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገልጿል፡፡

ኮንትሮባንድ በሀገር ኢኮኖሚ ላይም ሆነ በህበረተሰቡ ጤና ላይ የሚደርሰው ጉዳት የከፋ በመሆኑ ህበረተሰቡ ኮንትሮባንዲስቶችን በማጋለጥ ከምንጊዜውም በተሻለ መልኩ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡

ምንጭ ገቢዎች ሚኒስቴር

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *