ፈረንሳይ ከቴህራን ጋር ለመስራት የአሜሪካ ህግ አያስጨንቀኝም አለች
ፈረንሳይ ከቴህራን ጋር ለመስራት የአሜሪካ ህግ አያስጨንቀኝም አለች
አርትስ 30/02/2011
ፈረንሳይ አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን አዲሱን ማዕቀብ ወደ ጎን በመተው ከኢራን ጋር ያላትን የጋራ ግብይት ለማጠናከርና ቆርጣ መነሳቷን ተናግራለች፡፡
ፋይናንሺያል ታይምስ እንደዘገበው ፈረንሳይ አሜሪካ የዓለምን ንግድ በፈላጭ ቆራጭነት ለመምራት የምታደርገው ጥረት ማብቃት አለበት የሚል አቋሟን አሳውቃለች፡፡
የፈረንሳይ የኢኮኖሚ ሚኒስትር ቡሩኖ ሊ ሜይር የአውሮፓ ህብረት ዶላርን የሚገዳደር የዩሮ ግብይት ከኢራን ጋር ለመመስረት ልዩ የፋይናንስ መመሪያ ዕቅድ እያወጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሚንስትሩ አክለውም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የማንንም ፈቃድ ሳይጠይቁ የራቸውን የንግድ ነፃነት ማረጋጥ አለባቸው ለዚህም ጠንክረው እየሰሩ ነው ብለዋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራኑን የኒውክሌር ስምምነት ረግጠው ከወጡ ወዲህ ከሩሲያና ከቻይና ጋር በመሆን ስምምነቱ እንዲቀጥል በትብብር እየሰራ ይገኛል፡፡
አዲሱ የትራምፕ ማዕቀብ በኢራን ላይ በተጣለ ማግስት ቱርክ፣ እንግሊዝና ኖርዌይ ከኢራን ጋር ለሚያደርጉት የንግድና ኢኮኖሚ ትብብር የአሜሪካ ህግ እንደማይገዛቸው በግልፅ መናገራቸው ይታወሳል፡፡