ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገር ሉዓላዊነት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባቸው ተገለጸ::
አዲስ አበባ፣ግንቦት 18፣2012 ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገር ሉዓላዊነት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባቸው ተገለጸ::
“የኢትዮጵያ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች ሚና ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግደብ ግንባታ ሁለንተናዊ ድጋፍ እና ተሳትፎ” በሚል መሪ ቃል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዳራሽ ውይይት ተደርጓልበውይይቱ ወቅት በሀገሪቱ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች በሀገር ሉዓላዊነት እና አንድነት ጉዳይ እንደማይደራደሩ ተናግረዋል።
በተለያዩ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ልዩነት ቢኖርም በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ግን ምንም አይነት ልዩነት ሳይኖር በጋራ ድጋፍ እንደሚያደርጉም ኢቢስ ዘገቧል ።ፖለቲካ ሊኖር የሚችለው የሀገር ሉአላዊነት እና ጥቅም ሲከበር መሆኑን ያነሱት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎቹ የትኛውም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲ በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ የተለሳለሰ አቋም ሊያራምድ አይገባም ብለዋል።