ህንድ የአቡዳቢን እርዳታ አልፍልግም አለች፡፡
የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ህንድ ያጋጠማትን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ 100 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ገንዘብ ለመለገስ ተዘጋጂታ ነበር፡፡
ይሁን እንጂ ህንድ ምንም እንኳ በአደጋው 400 ዜጎቿ ህይዎታቸውን ቢያጡና በሚሊዮን የሚቆጠሩት ቢፈናቀሉባትም እርዳታውን አልቀበልም ብላለች፡፡
የህንድ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በሰጠው መግለጫ እንዳሳታወቀው የሀገሪቱ ፖሊሲ እንዲህ ዓይነት የተፈጥሮ አደጋ ባጋጠመ ጊዜ የመልሶ ማቋቋሙን ሰስራ በራሷ አቅም እንድትወጣው ስለሚያስገድድ ነው እርዳታውን ያልተቀበለችው፡፡
ህንድ በአደጋው ሳቢያ ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ኪሳራ እንደደረሰባት ሚድል ኢስት ሞኒተር በዘገባው አስነብቧል፡፡