ህጋዊ የጉዞ ፈቃድ ሳይኖራቸው ወደ ታንዛንያና ሊቢያ የገቡ 65 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ
አርትስ 10/04/2011
በታንዛንያ መንግስት ህጋዊ የጉዞ ፈቃድ ሳይኖራቸው የገቡ 231 ኢትዮጵያውያን ክሳቸው ተቋርጦ ምህረት አንዲያደርግላቸው በተደረገ ጥረትዛሬ 65ቱ ወደ ሀገራቸው ገብተዋል ፡፡
ቀሪዎቹ ከኢትዮጵያ አየርመንገድና ከዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት (አይ.ኦ.ኤም) ጋር በመተባበር ወደሀገራቸው እንዲገቡ ይደረጋል ተብሏል፡፡
እንደውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ገለፃ ካይሮ የሚገኘው የኢትዮጲያ ኢምባሲ ሊቢያ ከሚኖሩ ሌሎች በጎ አድራጊኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት (አይ.ኦ ኤም) ጋር በመተባበር ዜጎች ወደሀገራቸው እንዲመሉ እያደረገ ነው፡፡
በተመሳሳይ ካርቱም ሱዳን የሚገኘው የኢትዮጲያ ኤምባሲ ከአገሪቱ ፖሊስ ጋር በመተባበር በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ታግተው የነበሩ 15ኢትዮጵያውያንን ከታሰሩበት አስፈትቷል፡፡