loading
ለሕዳሴዉ ግድብ የግንባታ ቁሳቁሶችን በወቅቱ ለማድረስ የትራንስፖርት እጥረት

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19፣ 2013  የሕዳሴዉ ግድብ ሁለተኛ ምዕራፍ የውሃ ሙሌት ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል የሲሚንቶና ሌሎች የግንባታ ቁሳቁሶችን በወቅቱ ለማድረስ የትራንስፖርት ችግር መከሰቱ ተገለፀ፡፡

ይህ የተገለጸዉ  የታላቁ  የኢትጵያ  ህዳሴ ግድብ ሁለተኛውን የውሃ ሙሌት ለማሳካት የከባድ ጭነት ባለንብረቶች የ24 ሰዓት የስራ ርብርብ ተሳታፊ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌደሬሽን ጥሪ ባቀረበበት ወቅት ነዉ ሲሚንቶ እና ሌሎች የግንባታ ቁሳቁሶችን ለማጓጓዝ ከዚህ ቀደም አገራዊ ሃላፊነታቸውን ሲወጡ የነበሩ የትራንስፖርት ድርጅቶች እና ማህበራት ዛሬም የታላቁ ህ ዳሴ ግድብ ሁለተኛው ምዕራፍ ሙሌትን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል የበኩላቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል።

የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ብርሀኑ ዘርዑ በግንባታው ሂደት  ወሳኝ  የሆነውን የሲሚኒቶና ሌሎች  ግብዓቶች  አቅርቦት በማቀላጠፍ  በኩል  የትራንስፖርት ማህበራትና ድርጅቶች አስፈላጊ  በሆነ መጠን  ባለመሳተፋቸው እና ባለመንቀሳቀሳቸው በአቅርቦት በኩል መቀዛቀዝ መኖሩን  ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡ለዚህም የጸጥታ ችግር በምክንያትንት ተነስቷል፡፡ፌደሬሽኑ  ማህበራቱ  የሚቀርብላቸውን የስራ ስምሪት  በመቀበል  ለግድቡ እውን መሆን የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቀርቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *