loading
ሊቨርፑሎች ዓመቱ የኛ ነው እያሉ ነው።

የሊቨርፑል ደጋፊዎች ክለባቸው የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ካነሳ ሃያ ስምንት ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም መጭው ዘመን የኛ ነው በማለት ሊጉ ከመጀመሩ በፊት እየፎከሩ ነው ይላል የ ዘሰን ዘገባ።
ይህን ተከትሎም የርገን ክሎፕ ከአምናው ሻምፒዮን ጋርዲዮላ በልጠው ለመገኘት ከአሁኑ ትልቅ የቤት ስራ ይጠብቃቸዋል።
ክሎፕ አስተያየታቸውን ሲሰጡም ማንቸተር ሲቲዎች የትኛውንም ክለብ የማሸነፍ ብቃት አላቸው፤ ቢሆንም ግን ከረጅም ጊዜ በኋላ የቀዮቹ ደጋፊዎች ይህን ክብር ሊመልሱ ይችላሉ ብለዋል።
የሊቨርፑል ስብስብ የዘንድሮውን ዋንጫ የማሳካት አቅም ያለው ስለመሆኑ ብዙዎቹ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ይደመጣሉ።
እናም ሊቨርፑሎች በጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ እየተመሩ የዘንድሮውን ዋንጫ የሚያነሱ ከሆነ ዩ ዊል ኔቨር ወክ አሎን የሚለው መዝሙር ከመችውም ጊዜ በላይ በመርሲሳይድ ከፍ ብሎ ይስማል ማለት ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *