loading
ልጆቿን የምታስርብ ሃገር ልትለማ አትችልም-ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 በህፃናት ምገባ ላይ ትኩረቱን ያደረገው ስኩል ሚል ኢኒሸቲቭ የተማሪዎችን የምግብ እጥረት ለመቅረፍ የድርሻችንን እንወጣ ሲል ጥሪ አቀረበ፡፡

ድርጅቱ ይህን ያለው በተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም የተሰሩትን ሥራዎች ማሳያና የምስጋና መርሐ ግብር ባካሄደበት ወቅት ነው።

የስኩል ሚል ኢኒሸቲቭ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው ሃገር የምትለማው ዜጎቿን ስትንከባከብ ነው ብለዋል።

ልጆች ባሉበት ሁሉ ምግብ ይኑር በሚል መሪ ሐሳብ የተመሠረተው ፕሮጀክት ስራውን ከ7 ዓመት በፊት የጀመረ ሲሆን ህጻናት ተማሪዎች በወተት ልማት ፕሮጀክት ታቅፈው እንዲመገቡ እያደረገ ይገኛል፡፡

ወይዘሮ ፍሬዓለም በተለያዩ ወረዳዎች በተለይም በዋግ ሰፊ ስራ መሰራቱን ተናግረው ለዚህ ሥራ መነሳሳት እና ጉዳዩን በትኩረት እንዲመለከቱት ያደረጋቸው የችግሩ ስፋት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በየትምህርት ቤቶቹ የሚታየው የተማሪዎች የምግብ እጥረት ፋታ የማይሰጥ የማኅበረሰብ ችግር መሆኑን ተገንዝበን ሁላችንም ባለድርሻዎች ለህጻናት ተማሪዎች ምግብ በመሥጠት ልንደርስላቸው ይገባልም ብለዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *