loading
መርማሪ ፖሊስ የስብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈፀምበት የነበረ ተጨማሪ ሚስጥራዊ የማሰቃያ እስር ቤቶችን ማግኘቱን ለፍርድ ቤት አስረዳ

አርትስ 18/04/2011

መርማሪ ፖሊስ በቀድሞ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሁለት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በነበሩ ማእሾ ኪዳኔ እና ሃዱሽ ካህሳይየምርመራ ሂደት ላይ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛው የወንጀል ችሎት ቀርቦ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ተጠርጣሪ ማእሾ ኪዳኔ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በተለያዩ ሀላፊነት ሲሰሩ በነበረበት ወቅት የተሰጣቸውን ስልጣን ወደጎንበመተው በዋና ወንጀል አድራጊነት መጠርጠራቸው ይታወቃል።

ተጠርጣሪው አሁን ካልተያዙት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የቀድሞ ሀላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር በመመሳጠር በህገ ወጥመንገድ በወቅቱ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የነበሩ ግለሰቦች ላይ ድብደባና ስቃይ እንዲሁም አስነዋሪ ተግባራትንበመፈፀም እንዲሁም በኬተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙና ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ የሚለውም ከተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት ውስጥተጠቃሽ ነው።

እንዲሁም ከሚያገኙት ገቢ በላይ ምንጩ ያልታወቀ ከፍተኛ ሀብት አፍርተው መገኘታቸውም ነው የተገለፀው።

2ኛ ተጠርጣሪ አቶ ሀዱሽ ካህሳይ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሲሰሩ በቁጥጥር ስር ባሉ ተጠርጣሪዎች ላይ የሰብአዊ መብትጥሰት ወንጀሎች እንዲፈፀሙ በማድረግ፣ወንጀሉ መፈፀሙን እያወቁ ለህግ አካል ባለማቅረብ እና ከሚያገኙት ገቢ በላይ ምንጩያልታወቀ ከፍተኛ ሀብት አፍርተው ተገኝተዋል በሚል ነው የተጠረጠሩት።

ፖሊስ ከዚህ ቀደም በተሰጠው የምርመራ ጊዜ ወቅት ያከናወናቸውን ስራዎችም ለፍርድ ቤቱ ያስረዳ ሲሆን፥ በዚህ ወቅትም ከአምስትሰዎች ተጨማሪ የቃል ምስክር መቀበሉን አስታውቋል።

ሲሰሩበት ለነበሩበት መስሪያ ቤትም የነበሩበትን የስራ ሀላፊነት ለመለየት ደብዳቤ ልኮ ውጤት መቀበሉንም ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

በተጨማሪም ከዚህ በፊት ከተጠቀሱት ሚስጥራዊ የማሰቃያ እስር ቤቶች በተጨማሪ አንድ አዲስ ሚስጥራዊ የማሰቃያ እስር ቤትማግኘቱንም አስታውቋል።

መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የምስርክ ቃል መቀበል፣ የተጎዱ ዜጎችን የህክምና ውጤት መቀበል፣ ለመስሪያ ቤቶች የተጻፉ ደብዳቤዎችንማሰባሰብ እና የምርመራ ቡድን በማቋቋም በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ከሚገኙ ተጎጂዎች የቃል ምስክርነት መቀበል እንደሚቀረው ገልጿል።

ለዚህም ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛው የወንጀል ችሎት ጠይቋል፤ፍርድ ቤቱ መርማሪ ፖሊስ ከጠየቀው ውስጥ የ10 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፍቅዷል።ዘገባዉ የፋና ነዉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *