loading
መከላከያ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ተሸንፏል

አርትስ ስፖርት 20/03/2011

በካፍ ቶታል ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የወከለው መከላከያ በቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ለማድረግ ወደ ናይጀሪያአቅንቶ ኢኑጉ ላይ ከሬንጀርስ ኢንተርናሽናል ጋር ተጫውቶ 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡ የሬንጀርስ ኢንተርናሽናልን ሁለት የድል ግቦችበፍፁም ቅጣት ምት ያስቆጠረው አጉዳ ጎድዊን ነው፡፡

የጦሩ ቡድን ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ የመልሱን ጨዋታ አስቸጋሪ አድርጎበታል፡፡

አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከጨዋታው በኋላ በመ፣ህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳሰፈሩት ተጫዋቾቻቸው ያጋጠማቸዉን የዳኝነት ችግርተሸክመዉ ባሳዩት ብቃት መኩራታቸውንና እያንዳንዱ የጨዋታ እንቅስቃሴ ተጋጣሚያቸውን ሬንጀርስን በሚጠቅም መልኩ  እንደተዳኘ ነው የጠቀሱት፡፡

አሰልጣኙ በተለይ ሁለተኛው የተሰጠው ፍፁም ቅጣት ምት አግባብ ያለመሆኑን ጠቅሰው የተጋጣሚያቸውን ጥሩ ቡድንነትአድንቀዋል፡፡

የመልሱ ጨዋታ በሩዋንዳውያን ዳኞች እየተመራ በመጭው ዕሮቡ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ይደረጋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *