loading
ማንችስተር ሲቲ የካራባዎ ዋንጫ የፍፃሜ ተፋላሚውን ዛሬ ያውቃል

ማንችስተር ሲቲ የካራባዎ ዋንጫ የፍፃሜ ተፋላሚውን ዛሬ ያውቃል

የካራባዎ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ትናንት ምሽት በበርተን አልቢዮን እና ማንችስተር ሲቲ መካከል ተካሂዷል፡፡

በመጀመሪያው ዙር ኢቲሃድ ላይ 9 ለ 0 ያሸነፈው ሲቲ ወደ ፒረሊ ስታዲየም አቅንቶ በ1 ለ 0 ውጤት አሽንፏል ፤ በአጠቃላይ ውጤት ደግሞ 10 ለ 0 ረትቷል፡፡

በምሽቱ ግጥሚያ በሲቲ በኩል ፔፕ ጓርዲዮላ ለበርካታ ወጣት ተጫዋቾች ዕድል የሰጡ ሲሆን ብቸኛዋን የድል ግብ ሰርጂዮ ኩን አጉዌሮ በመጀመሪያው አጋማሽ ማስቆጠር ችሏል፡፡

በዚህም ዘ ሲቲዝንስ በተከታታይ ለሁለት ዓመት ለፍፃሜ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ዛሬ ምሽት 4፡45 ላይ ቼልሲ ስታንፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ላይ ቶተንሃምን ያስተናግዳል፡፡ በመጀመሪያው ጨዋታ ዊምብሌ ላይ ስፐርስ 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን ሰማያዊዎቹ ለፍፃሜ ለመብቃት 2 ለ 0 እና ከዚያ በበለጠ ውጤት ድል ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

የማውሪሲዮ ፖቼቲኖ ቡድን  ቁልፍ ተጫዋቾችን ሀሪ ኬን እና ደል አሊን በጉዳት እንዲሁም ሰን ሁንግ ሚንን በብሔራዊ ቡድን ግዴታ ምክንያት ግልጋሎት አያገኝም፡፡ በአንድ በኩል የሉካስ ሞራ እና ሙሳ ሲሶኮ ከጉዳት መመለስ ለክለቡ መልካም ዜና ሁኖ ተበስሯል፡፡

አዲሱ የቼልሲ ፈራሚ ጎንዛሎ ሂግዌን ዘግይቶ በመፈረሙ ምክንያት በዚህ ጨዋታ የማይሰለፍ ሲሆን  ኢዲን ሀዛርድ እና ኦሊቪዬ ጂሩ የፊት መስመሩን ይመሩታል ተብሏል፡፡

የዛሬው ምሽት የድምር ውጤት አሸናፊ በፍፃሜ ጨዋታ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ዊምብሌ ላይ የካቲት 17 ይፋለማሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *