loading
ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ

አርትስ 11/04/2011

 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

ምክር ቤቱ በዛሬው በመደኛ ስብሰባው የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል።

በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረቡትን ሪፖርትናየውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ከተወያየበት በኋላ በ33 ተቃውሞና በ4 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።

የማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮች ኮሚሽን በክልሎች የአስተዳደር ወሰንና በማንነት ጥያቄዎች ዙሪያ በተደጋጋሚ የሚነሱ ችግሮችን ሀገርአቀፍ በሆነ እና በማያዳግም መልኩ ለመፍታት የሚያስችል ነው ተብሏል።

እንዲሁም ከወሰን አስተዳደር ጋር ተያይዞ በብሄር ብሄረሰቦች መካከል የቅራኔ ምንጭ የሆኑ ችግሮችን ገለልተኛ በሆነ፣ ሙያዊ ብቃት ባለው እናሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍትሄ የሚያፈላልግ መሆኑም ተጠቅሷል።

ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሆነው ኮሚሽኑ አሳታፊ፣ ግልጽ፣ አካታችና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ከአስተዳደር ወሰኖች፣ ራስን በራስማስተዳደር እና ከማንነት ጋር የተያያዙ ግጭቶችን እና መንስኤዎቻቸውን በመተንተን የመፍትሄ ሀሳቦችን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የህዝብተወካዮች ምክር ቤት እና ለአስፈፃሚ አካላት የማቅረብ አላማ እንዳለውም ተገልጿል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *