ምክትል ከንቲባው የቦርድ አሰራርን እናስቆማለን አሉ
አርትስ 27/02/2011
ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ይህንን የተናገሩት ከከተማው አስተዳደር አመራሮች ጋር በነበራቸው የውይይት መድረክ ላይ ነው።
ምክትል ከንቲባው እንደተናገሩትበከተማው በርካታ የተዝረከረኩ እናየህዝብን ሃብት የሚያባክኑ አሰራሮች መኖራቸው ተረጋግጧል።
ከነዚህ መካከል ቦርድ እና ፕሮጀክት ፅ/ቤትዋናዎቹ ናቸው ብለዋል፡፡
አንድ ሰው እስከ 15 ተቋማት ላይ የቦርድ አባል የሚሆንበት አሰራር ለህዝብ ጥቅምይውል የነበረውን ሃብት ያለአግባብ እያባከነ መሆኑንም ከንቲባው ተናግረዋል።
በከተማዋ ለደመወዝ ክፍያ ከሚውለው ሃብት ውስጥ 1/4ኛ የሚሆነው ለቦርድ ክፍያወጪ የሚደረግ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው ከዚህ በኋላ ቦርድ የሚባል አሰራርአይኖርም ብለዋል።
በከተማዋ የሚገኙ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤቶችን በተመለከተ ሲናገሩም አብዛኞቹ የተቋቋሙበትን ጊዜ የጨረሱ እና በአመራሩበጎ ፍቃድ እድሜያቸውን ያራዘሙ ናቸውበማለት ተችተዋቸዋል።
በተመሳሳይ በዚህ ዘርፍም በርካታ ህዝብሃብት እየባከነ መሆኑን ገልጸው በቅርቡበከተማዋ የሚካሄደው አጠቃላይ ሪፎርምእነዚህን ችግሮች የሚቀርፍ ነው በማለትተናግረዋል፡፡