loading
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በሳዑዲዓረቢያ የኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ትምህርት ቤትን ጎብኙ

አርትስ 15/02/2011

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር  ደመቀ  መኮንን በሳዑዲዓረቢያ ቆይታ በሪያድ ከተማ የኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማር ሂደት ዙሪያ ከቦርድ አባላቱ ጋር ተወያይተዋል።
የቦርድ አባላቱ በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄ አንስተዋል።

ትምህርት ቤቱ በሚጠናከርበት አግባብ ዙሪያ በሚመለከታቸው አካላት ተገቢ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እንዳሳወቀው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር  ደመቀ ለትምህርት ቤቱ ተማሪዎች የማበረታቻ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ታዳጊ ህፃናት ደግሞ መዝሙር እና አዝናኝ ትርዒትአቅርበዋል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *