ሩሲያና ዩክሬን ወደ አዲስ ፍጥጫ ገብተዋል
አርትስ 17/03/2011
የሩሲያ ጦር ሀይል በክሬሚያ ድንበር አካባቢ ሶስት የዩክሬን ወታደራዊ መርከቦችን ማርኳል የሚሉ ዘገባወች በስፋት እየተሰራጩ ነው፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው ሞስኮ ይህን እርምጃ የወሰደቸው የዩክሬን የጦር መርከቦች የተሰጣቸውን ማጠንቀቂያ ቸል ብለው ህገ ወጥ እንቅስቃሴ በማድረጋቸው ነው፡፡
የሩሲያ ብሄራዊ የደህንነት አገልግሎት የጦር መርከቦቹ በጥቁር ባህር የሩሲያን የባህር ድንበር ጥሰው በመግባታቸው እርምጃውን ለመውሰድ ተገደናል ብሏል፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ፔትሮ ቦሮሸንኮ ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ከፍተኛ ወታራዊ ባለ ስልጣኖቻቸውን ሰብስበው ስለሁኔታው ምክክር አድርገዋል፡፡
የዩክሬን ባህር ሀይል እንዳስታወቀው ከሩሲያ የጦር መርከቦች በተተኮሰ መሳሪያ ስድስት መርከበኞቹ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በሩሲያ ጠያቂነት በጉዳዩ ዙሪያ ሊመክር እንደሆነም ተሰምቷል፡፡