loading
ሩሲያ አሜሪካ በዩክሬኑ ጦርነት ቀጥተኛ ተሳታፊ ናት ስትል ከሰሰች፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 ሩሲያ አሜሪካ በዩክሬኑ ጦርነት ቀጥተኛ ተሳታፊ ናት ስትል ከሰሰች፡፡ ይህ የሞስኮ ወቀሳ የተሰማው የዩክሬን ወታደራዊ መረጃ ምክትል ሃላፊ ቫዲም ስኪቢትስኪ ከአሜሪካ የተበረከተላቸው የረዥም ርቀት የሮኬት ማስወንጨፊያ ስርዓቶች በጥሩ የሳተላይት ምስል እና እውነተኛ መረጃ አቀባይ መሆናቸውን ከገለፁ በኋላ ነው፡፡


ምክትል ሃላፊው ከቴሌግራፍ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ ከጥቃቱ በፊት በአሜሪካ እና በዩክሬን የስለላ ባለስልጣናት መካከል ምክክር የነበረ ቢሆንም የዋሽንግተን ባለስልጣናት በሚፈለጉት ኢላማዎች ላይ መረጃዎች እየሰጡን አይደለም ብለዋል። ዋሽንግተን ሚናዋን በጦር መሣሪያ አቅርቦት ላይ ብቻ መገደቧን በተደጋጋሚ ብትገልጽም ቃለ መጠይቁ ግን ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆኗን ያመላክታል ብሏል። በሮኬት ጥቃቶች በዶንባስ እና በሌሎች ክልሎች ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ላይ ለሚደርሱ የሰላማዊ ሰዎች የጅምላ ሞት፤ የመኖሪያ አካባቢዎች እና መሠረተ ልማቶች ውድመት ቀጥኛ ተጠያቂው የባይደን አስተዳደር ነው ሲል የሩሲ መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።


ይህን ዘገባ አልጄዚራ እስካጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ከዋይት ሀውስ አሊያም ከፔንታጎን ለቀረበው የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር ውንጀላ ምላሽ አልተሰጠም።
ዩክሬን እና ምዕራባውያን ሀገራት ሩስያ በየቀኑ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠሩ አውዳሚ የሚሳኤል ጥቃቶችን ትፈጽማለች በማለት ቢከሱም ሞስኮ በበኩሏ ሆን ብላ በእነዚህ ወገኖች ላይ ጉዳቶችን እንደማታደርስ ትናገራለች።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *