loading
ሪክ ማቻር ለሰላም ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋገጡ

ሪክ ማቻር ለሰላም ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋገጡ

አርትስ 22/02/2011

 

የደቡብ ሱዳን አማጺያን መሪ ሪክ ማቻር ለተፈረመው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋገጡ።

በጁባ በተካሄደው የሰላም ስነስርዓት ላይ የአማጺያኑ መሪ ጦርነት ባደቀቃት ሃገራቸው ለሰላም እድል ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ማቻር በነጻነት አደባባይ በተካሄደው ስነስርዓት ላይ ለተሰበሰበው ህዝብ እንደተናገሩት እዚህ የተገኙት ሰላምን ለማረጋገጥ ነው። የምንፈልገው ሰላምና አነድነት ነው ብለዋል።

እስር ቤት የታጎሩ የፖለቲካ እስረኞችን እንዲፈቱም በዚሁ አጋጣሚ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪርን  ጠይቀዋል።

አዲሱ የሰላም ስምምነት የፌዴራል መንግስትን ለማዋቀር እንደሚረዳም ማቻር ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *