ሱዳን ዋና ከተማዋን ካርቱምን በአንድ ጊዜ ሊያጠፋ የሚችል ተቀጣጣይ ፈንጂ መያዟን አሰታወቀች::
አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 ሱዳን ዋና ከተማዋን ካርቱምን በአንድ ጊዜ ሊያጠፋ የሚችል ተቀጣጣይ ፈንጂ መያዟን አሰታወቀች:: የሀገሪቱ ባለ ስልጣናት እንዳሉት ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 41 ሰዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡
የሱዳን መንግስት አቃቤ ህግ ታጌልሲር አል ሄብር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፈንጂው ባይያዝና ቢፈነዳ ኖሮ የካርቱምን ከተማ ሙሉ በሙሉ የማጥፋት አቅም እንደነበረው ተናግረዋል፡፡ አፍሪካ ኒወስ እንደዘገበው የአቃቤ ህግ ቢሮ ከተቀጣጣይ ፈንጂው ገሰር ግንኙነት አላቸው ተብለው በተጠረጠሩት ግለሰቦች ላይ አስቸኳይ ምርመራ ጀምሯል፡፡
የደህንነት ሰዎች ከነሀሴ ወር ጀምሮ በሀገሪቱ የሽብር ቡድኖች እንቅቃሴ መኖሩ መረጃ ደርሷቸው ስለነበር ጥብቅ ክትትል ሲያደር መቆየቱ ተነግሯል፡፡ የሱዳን የመከላከያ ፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይል ቃል አቀባይ ጀማል ጁማዓ አንዳንድ ግለሰቦች በተለያዩ መንገዶች ከወንጀለኞች ጋር በመተባበር ጥፋት እንዲደርስ እንደሚያደርጉ ደርሰንበታል ብለዋል፡፡
ጁማዓ አክለውም ሁኔታው ሀገራችን በመንግስታት በሚደገፍ የሽብር እንቅስቃሴ ዳግም እንዳትፈረጅ ትልቅ ስጋት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ሱዳን እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ1993 ጀምሮ በአሜሪካ የሽብር መዝገብ ውስጥ ስሟ መስፈሩ ይታወቃል፡፡