loading
ሶሪያ ውስጥ በሚካሄደው ጦርነት ግማሽ ሚሊዮን ህፃናት ህይዎታቸው አደጋ ላይ ነው ተባለ

አርትስ 2/1/2011
ይህን ያለው ዓለም አቀፉ የህፃናት አድን ድርጂት ነው፡፡ ድርጂቱ እንዳለው በአሁኑ ወቅት ሶሪያ ውስጥ ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህጻናት ለህይወታቸው አስጊ የሆነ የምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች እነዚህን ህፃናት ለመታደግ የሚያስችል ድጋፍ ለማድረግ ከፍተኛ የገንዘብ እጥረት አለባቸው፡፡
የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሄሊ ቶርኒንግ ሽሚደ በአሁኑ ወቅት እንደ ሶሪያ፣ የመን እና ደቡብ ሱዳን ባሉ ሀገሮች ርሀብ ዋነኛ የጦር መሳሪያ ሆኖ እያገለገለ ነው ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *