loading
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ዋንጫ ውጭ ሆነ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ዋንጫ ውጭ ሆነ

 

በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ (የኢትዮጵያ ዋንጫ) የአንደኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም አንድ ግጥሚያ ተካሂዷል፡፡

ባለፉት ጥቂት አመታት በጥሎ ማለፉ ዋንጫ ጥሩ ስኬትን እያስመዘገበ የሚገኘው መከላከያ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫውተው፤ የጦሩ ቡድን  በሁለተኛው የጨዋታው አጋማሽ 52ኛ ደቂቃ ላይ ቴውድሮስ ታፈሰ በቅጣት ምት ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 አሸንፎ ወደ ተከታዩ ዙር ተሻግሯል፡፡

ፈረሰኞቹ በሙሉ ጨዋታው ከመከላከያ በበለጠ የግብ ሙከራዎችን ማድረግ ቢችሉም ወደ ጎል ግን መቀየር አልቻሉም፡፡ በተለይ በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ስድስት የግብ አጋጣሚዎችን ቢያገኙም አልተጠቀሙባቸውም፡፡

ጊዮርጊሶች ግብ ካተናገዱም በኋላ  በተደጋጋሚ ወደ መከላካያ የግብ ክልል መድረስ ቢችሉም፤ በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሚመራው ቡድን መረቡን ሳያስደፍር ወጥቷል፡፡ ቡድኑም በኢትዮጵያ ዋንጫ ባለፉት አመታት ባሰመዘገባቸው ውጤቶች ለውድድሩ የተሰራም አስመስሎበታል፡፡

በቀጣይ መከላከያ በሩብ ፍፃሜው የመቐለ 70 እንደርታን እና ደቡብ ፖሊስን አሸናፊ ጋር ይጫወታል ተብሏል።

በነገው ዕለት በትግራይ ስታዲየም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከ ፋሲል ከነማ በ9፡00 ሰዓት ይጫወታሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *