loading
በሊቢያ የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ ነው፡፡

በሊቢያ የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ ነው፡፡

በተባበሩት መነግስታት ድርጅት እውቅና የተሰጠው የሊቢያ መንግስት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ  በጄኔራል ሀፍታር ላይ እርምጃ እንዲወስድ እየተማፀ ነው ተብሏል፡፡

በምስራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል የሚንቀሳቀሰው የጄኔራል ሀፍታር ጦር ትርፖሊን ለመያዝ ከመንግስት ወታሮች ጋር በሚያደርገው ውጊያ እስካሁን የሞቱ ሰዎች ቁጥር 205 መድረሱ ተነግሯል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው በግጭቱ ምክንያት በየቀኑ አካባቢያቸውን ለቀው የሚሰደዱ ሊቢያዊያን ቁጥርም በየጊዜው እየጨመረ ነው፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ጦርነቱ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ቁስለኞችን ለማከም  የጤና ባለሞያዎችን አሰማርቻለሁ ብሏል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *