loading
በመጭው እሁድ 5ኛው የ30 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በቢሾፍቱ ይደረጋል

በመጭው እሁድ 5ኛው የ30 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በቢሾፍቱ ይደረጋል

አርትስ ስፖርት 05/04/2011

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውድድሩን እስመልክቶ በሰጠው መግለጫ የቴክኒክ ኃላፊው አቶ ዱቤ ጅሎ የውድድሩ መካሄድ ለአትሌቶች የውድድር እድል ለመፍጠር እና ለማራቶን ተወዳዳሪዎች ደግሞ ጠቀሜታ እንዳለው  ተናግረዋል፡፡

በውድድሩ ከሶስት ክልሎች፣ ሁለት ከተማ አስተዳደሮች፣ አስራ አራት ክለቦችና ተቋማት እንዲሁም በግል የሚሳተፉ አትሌቶችን ጨምሮ በሁለቱም ፆታ በቁጥር 419 ይደርሳሉ ተብሏል፡፡ ለአሸናፊ አትሌቶች የሜዳሊያና ገንዘብ ሽልማት የሚበረከትላቸው ሲሆን በአጠቃላይ 250 ሺ ብር ለውድድሩ ተመድቧል፡፡

ብሄራዊ አትሌቶች ሀገራቸውን በሚወክሉበት ጊዜ የነበረው የአትሌቶች መምረጫ መስፈርትን በተመለከተ ፌዴሬሽኑ ከአትሌቶች ማናጀሮችና ወኪሎች፣ አሰልጣኞችና ክለቦች ጋር ውይይት አድርጎ ስምምነት ላይ መድረሱን አቶ ዱቤ ተናግረዋል፡፡

በመግለጫው ፌዴሬሽኑ ብሄራዊ የአትሌቶች ምርጫን ከ50 ዓመታት በላይ በአንድ መዕከል ውስጥ አትሌቶችንና አሰልጣኞችን በመመምጥ ሲሰራ የቆየ ሲሆን ከ2010 ጀምሮ ግን የብሄራዊ ቡድን ተመራጮች እዛው ባሉበት፤ በክለብ፣ ክልል፣ አካዳሚ፣ ማናጀር እንዲሁም በግል እንዲሰለጥኑ አስፈላጊው ክትትልና ድጋፍም በዛው እንዲደረግ መወሰኑም ተነስቷል፡፡

በብሔራዊ ቡድን በሁለቱም ፆታ 230 አትሌቶች ተይዘዋል የተባለ ሲሆን የዋና እና ምክትል አሰልጣኞች ሹመትን በተመለከተ በብዛት ያስመረጠው ክለብ፣ ክልል አሊያ አካዳሚ ያስመርጣል አሊያም ፌዴሬሽኑ ብቃታቸውን ገምግሞ እንደሚቀጥር አስታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *