loading
በሙስና ወንጀሎች ላይ የተጀመረው ምርመራ በሜቴክ ብቻ የሚያቆም አይደለም አለ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ

አርትስ 14/03/2011

ተቋሙ የቀጣይ መቶ ቀናት የስራ ዕቅዱን አስመልክቶ  ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ  በሌብነትና የሙስና ወንጀሎች ላይ የተጀመረው ምርመራ በብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ላይ ብቻ ታጥሮ የሚቆም ሳይሆን ሌሎችንም ግዙፍ ፕሮጀክቶች የሚያዳርስ ነው ብሏል።

እንደ ፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ  የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እና ህግን ለማስፈን የሚሰሩ ሰራዎች  እና ምርመራዎች  ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

የጠቅላይ ዐቃቢ ህግ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱና  በሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ የተለየ ምርመራ እየተካሄደ ነው።

የምርመራው ውጤት እንዳለቀም ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ብለዋል።

ሃላፊው ምርመራ እየተካሄደባቸው የሚገኙትን ድርጅቶች ስም ከመጥቀስ ተቆጥበዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *