loading
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፈሪካውያን መጠለያቸውን የማጣት ስጋት ላይ ናቸው ተባለ

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፈሪካውያን መጠለያቸውን የማጣት ስጋት ላይ ናቸው ተባለ

ከሰሃራ በታች የሚገኙት አፍሪካዉያን ላይ መጠለያቸውን የማጣት ስጋት እንዳለ የተጠቆመው አዲስ በወጣ የዳሰሳ ጥናትነዉ፡፡

ጥናቱ ከሰሃራ በርሃ በታች በሚገኙ ሀገራት 10 ሚሊዮን የከተማ ነዋሪዎች፤ ያለፈቃዳቸው ከቤት ንብረታቸው የመፈናቀል ስጋት ላይ መዉደቃቸዉን ገልጿል፡፡

አጠቃላይ ጥናቱ የደቡብ ምስራቅ ኤስያ፣ ላቲን አሜሪካ፣ ሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ፤ አውሮፓ ዩናይትድ ኪንግደም አካልሏል ተብሏል፡፡ ጥናቱ በተደረገባቸዉ  18 ሀገራት በከተማ የሚኖሩ 32 ሚሊዮን ጎልማሶች፤ ከቤታቸው እና መሬታቸው ላይ ለመሰንበታቸው እርግጠኛ አይደሉም፡፡

ጥናቱ ጨምሮ ይህ የመፈናቀል ልማድ የሚቀጥል ከሆነ እ.አ.አ በ2050  ከ210 ሚሊዮን ለሚልቁ ዜጎች የመከራ ጊዜን ያስከትላል ይላል፡፡

በግኝቱ በሚቀጥሉት አምስት አመታት፤ ከ33 ሀገራት ውስጥ ከአራት ጎልማሳዎች አንዱ መጠለያውን ያጣል አሊያ የማጣት ደረጃ ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የዳሰሳ ጥናቱ Prindex በተባለ ጥናት አድራጊ ድርጅት፤ Global Land Alliance እና ለንደን ላይ ተቀማጭነቱን ባደረገው Overseas Development Institute በተባሉ ሁለት የዳሰሳ ጥናቱ አማካሪ ቡድኖች   አነሳሽነት፤ ከOmidyar Network በተገኘ ድጋፍ መካሄዱን ኦል አፍሪካ ዶት ኮም ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *