loading
በማላዊ በተከሰው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ጨምሯል፡፡

በማላዊ በተከሰው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ጨምሯል፡፡

በደቡባዊ የማላዊ አካባቢ የዘነበው አውሎ ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ 56 ሰዎችን ሲገድል 577 የሚሆኑትን ደግሞ ለጉዳት ዳርጓል፡፡

ከሳምንታት በላይ የዘለቀው ከባድ ዝናብ እና አውሎ ነፋስ ወንዞች ግድባቸውን ጥሰው እንዲፈስሱ በማድረጉ የተነሳ ነው አደጋው የደረሰው ተብሏል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው እስካሁን የመኖሪያ አካባቢያቸው በጎርፍ በመጥለቅለቁ ሳቢያ 83 ሺህ ሰዎች ቀያቸውን ለቀው ወደ ሌላ አካባቢዎች ለመሰደድ ተገደዋል ፡፡

የማላዊ የአደጋ መከላከል አስተዳደር ቃል አቀባይ ቺፒሊሮ ካሙላ ተፈናቃዮቹ በ187 ጊዜያዉ መጠለያ ካምፖች ተሰባስበው ድጋፍ እየተደረገላቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የሀገሪቱ የሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ድርጅት በቀጣዮቹ ቀናትም ሁኔታው እንደሚቀጥል እና ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡

በተለይ በጎረቤት ሞዛምቢክ ድንበር ቤራ በተባለው አካባቢ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል ነው ትንበያው የሚያሳየው፡፡

የማላዊ ፕሬዝዳንት አርተር ፒተር ሙታሪካ የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ በሀገሪቱ ያወጁ ሲሆን ወደ ሰሜናዊ ማላዊ ሊያደርጉት የነበረውን የስራ ጉዞም አደጋው የደረሰበትን አካባቢ ለመጎብኘት ሲሉ ሰርዘውታል ተብሏል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *