loading
በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል አዲስ የሰላምና ትብብር ምዕራፍ መፈጠሩን የኢጋድ ሊቀመንበር ዶ/ር አብይ አህመድ ገለጹ፡፡

አርትስ 03/01/2011
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) 33ኛው የመሪዎች ልዩ ስብስባ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ዶ/ር አብይ አህመድ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በቀጠናው ሀገራት መካከል አዲስ የሰላምና ትብብር ምዕራፍ መፈጠሩን ገልጸዋል ፡፡
ለደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደት ስኬት ድጋፍ እያደረጉ ላሉት ባለድርሻ አካላትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡
የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎችም የኢጋድ መሪዎቹ ባቀረቡት የሰላም ሰነድ ላይ ፊርማቸውን አሳርፈዋል፡፡
የዉጭ ጉዳይን ጠቅሶ ኢቢሲ እንደዘገበዉ በስብሰባው ላይ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ፣ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ፣ የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኦማር ጊሌ ፣ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂና ሌሎች የደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደት ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *