በረሺድ ጥላይብ መመረጥ ዌስት ባንክ ደስ ብሏታል፡፡
በአሜሪካ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሙስሊም ሴት የኮንግረስ አባል በመመረጣቸዉ በዌስት ባንክ ያሉ ቤተሰቦቻቸዉ ደስታቸዉን አየገለጹ ነዉ፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበዉ የጥላይብ ሴት አያት ፣አክስትና እንዲሁም አጎቶችዋ የተሰማቸዉን ደስታ ተሰብስበዉ ገልጸዋል፡፡
አንድ ቀን እንዲህ እንደምታኮራን እናምን ነበር ብለዋል፡፡
የጥላይብ ቤተሰቦች የሚኖሩበት ዌስት ባንክ ከ1967 ጀምሮ በእስራኤል ቁጥጥር ስር ይገኛል፡፡
ቤተሰቡ የጥላይብ የኮንግረስ አባል ሆኖ መመረጥ በአከባቢያቸዉ ስላለዉ ችግር ድምጻቸዉ እንዲሰማ ምክንያት እንደሚሆንም ተስፋ አላቸዉ፡፡