በርሊን የኢራን አየር መንገድ ወደ ሀገሯ እንዳይበር አገደች
በርሊን የኢራን አየር መንገድ ወደ ሀገሯ እንዳይበር አገደች
ጀርመን ይህን እርምጃ ለመውሰድ የተገደደቸው ከስለላ ጋር በተያያዘ ምክንያት መሆኑን ደይሊ ስታር በዘገባው አስነብቧል፡፡
የጀርመን ከፍተኛ ባለ ስልጣናት ማሃን የተባለው የኢራን አየር መንገድ ለስለላ እና ለወታደራዊ ሚስጥር አገልግሎት እንደሚውል ጥርጣሬ አለን ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡
አየር መነገዱ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2011 አሜሪካ ማእቀብ ከጣለችባቸው የኢራን ተቋማት መካከል አንዱ ነው፡፡
አብዛኞቹ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ኢራንን በአህጉሩ የስለላ ተግባር ከመፈፀም አልፋ ጥቃት ለማድረስ እቅድ እንዳላት በመግለፅ ተደጋጋሚ ክሶችን ያቀርቡባታል፡፡
በዚህ ወር መጀመሪያ የአውሮፓ ህብረት በኢራን የደህንነት ተቋም እና በሁለት ከፍተኛ አመራሮች ላይ ያነጣጠረ ማእቀብ ጥለዋል፡፡
የማእቀቡ መነሻ ደግሞ ቴህራን በኔዘርላንድ፣ ዴንማርክ እና ፈረንሳይ የሚኖሩ በሮሃኒ መንግስት ላይ ትችት የሚሰነዝሩ ኢራናዊያን ላይ በፈጸመችው ግድያ እና የታቀደ ጥቃት ነው፡፡
ማና በሳምንት አራት ጊዜ ከቴህራን ወደ ደሰልዶርፍ እና ሙኒክ የጀርመን ከተሞች በረራ የሚያደርግ ግዙፍ አየር መንገድ መሆኑ ይታወቃል፡፡