በቅርቡ እጣ የወጣባቸው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለ እድለኞች እንዳይተላለፉ በፍርድ ቤት ታገዱ
በቅርቡ እጣ የወጣባቸው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለ እድለኞች እንዳይተላለፉ በፍርድ ቤት ታገዱ
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 8ኛ የፍትሃብሄር ችሎት በቅርቡ እጣ የወጣባቸው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለእድለኞች ስመ ሀብት/ካርታ/ እንዳይተላለፍ አገደ።
ፋና እንደዘገበዉ የጋራ መኖሪያ ቤቱን ለማግኘት ተመዝግበው 100 በመቶ የከፈሉ 98 ዜጎች ክስ መመስረታቸውን ተከትሎ ነው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ የፍርድ ሂደቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለባለ እድለኞች እንዳይተላለፉ ያገደው።