loading
በቆቦ ሆስፒታል አንዲት እናት 4 ልጆችን በሰላም ተገላገሉ

አርትስ 22/04/2011

መንታ መውለድ የተለመደ ቢሆንም በራያ ቆቦ ወረዳ አረቋቴ በተባለ ቦታ ግን አንዲት እናት አራት ልጆችን በሰላም መገላገላቸውን  ከፋና  ሰምተናል፡፡

ግለሰቧ ወይዘሮ እናት ሲሳይ የሚባሉ ሲሆን፥ ቅዳሜ በቆቦ ሆስፒታል በተደረገላቸው ክትትል ነው የወለዱት ተብሏል፡፡

እናት ከወለዱዋቸው አራት ህጻናት መካከል ሶስቱ ሴቶች ሲሆኑ፥ አንዱ ወንድ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ሐኪሞቹ ሦስቱ ህጻናት በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰው፥ አንደኛው የህክምና ክትትል እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል፡፡

እናት ሲሳይ ከተገላገሉ በኋላ እንደተናገሩት አራቱን ህጻናት የማሳደግ አቅሙ  የላቸዉም፡፡

መንግስትና በጎ አድርጊ ድርጅቶች እንዲሁም ግለሰቦች ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *