በቢሾፍቱ ከተማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ ነው ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ ከተማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ለፋና እንደተናገሩት ፥ አዲስ የሚገነባውን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለማስጀመር እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው።
አውሮፕላን ማረፊያውን ለመገንባት የሚያስፈልገውን የቦታ ጥያቄ ለመፍታት ከኦሮሚያ ክልል ጋር ምክክር እየተደረገ መሆኑን አቶ ተወልደ ተናግረዋል።
ሊገነባ የታሰበው ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሁሉንም አገልግሎቶች የሚሰጥ የራሱ ሆቴልም ይኖረዋል ተብሏል።
አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በአመት ከ80 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑንም ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።